The Africa Day Initiative successfully held its first-panel discussion. Scholars from various higher education institutions, stakeholders working on African unity, journalists, and guests participated in the panel discussion.

አፍሪካ ዴይ ኢኒሼቲቭ ካቀዳቸዉ ተግባራት የመጀመሪያ የሆነዉን የፓናል ዉይይት በተሳካ ሁኔታ አካሂዷል። በፓናል ዉይይቱ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተገኙ ምሁራን፣ በአፍሪካ አንድነት ዙሪያ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት፣ ጋዜጠኞችና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳትፈዋል።

በእለቱ የአፍሪካ ሃገራት የነጻነት ጉዞንና የፓን አፍሪካኒዝምን የትግል ሂደት የሚያስታዉሱ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዉ ዉይይትና ጥያቄና መልስ ተደርጎባቸዋል፣

Key speakers

የእለቱ ጽሁፍ አቅራቢዎችም፣ 

Mr. Yeshiwas Asefa has had a lengthy political career in Ethiopia and has fought and continues to fight for the stability and unity of his nation.

አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ረጅምና ጉዞ ያደረጉና ለሃገራቸዉ ሰላምና አንድነት ሲታገሉ የኖሩ፣ እየታገሉ ያሉ

Mr. Mulugetta Ketema is the son of Mr. Ketema Yifru, one of emperor Haile Selassie’s closest advisors and Ethiopia’s Minister of Foreign Affairs at the time, and the man who made the greatest contribution to the formation of the continental organization during the reign of the emperor. His son Mulugetta is an engaged observer and researcher of conflicts across the African continent.

አቶ ሙሉገታ ከተማ ይፍሩ፣ በንጉሱ ዘመን የአፍሪካ አንድነትን በመመስረቱ ሂደት ከፍተኛዉን ድርሻ ያበረከቱት የወቅቱ የኢትዮጵያ ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የንጉሱ የቅርብ አማካሪ ልጅ፣ በአፍሪካ አንድነት ዙሪያ በሚደረጉ ትግሎች ሁሉ ግምባር ወደም ተሳታፊና አጥኝ

Professor Ayele Bekri has written numerous books globally and has conducted in-depth research on Ethiopian and African history as well as the Ethiopian alphabet. 

ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፣ በአፍሪካ ፣ በኢትዮጵያ ስነጽሁፍና ፊደላት ዙሪያ ረጅም ጥናትን ያደረጉና በርካታ መጻህፍትን በአለም አቀፍ ደረጃ ያሳተሙ